ከ 80 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች የሚጠቀሙበት፣ Brave (ብሬቭ) የበይነመረብ አሳሽ እና መፈለጊያ፣ የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሚስጥራዊነት ያለው የበይነመረብ መረጃን ያቀርባል። አብሮ በተሰራው የማስታወቂያ ማገጃ እና VPN አማካኝነት፣ ድህረ ገፅ ላይ መረጃ በምትፈልጉበት ጊዜ፣ Brave ዱካ ተከታይ ሶፍትዌሮችን እና ማስታወቂያዎችን በራሱ ጊዜ ያግዳል።
አዲስ፡- በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ
ብሬቭ፣ ብሬቭ ሊዮ የተባለ የድህረ ገፅ መረጃ ሚስጥራዊነት መጠበቂያ ሥራ ላይ አውሏል። ሊዮ በበይነመረብ አሳሽ ላይ የሚገኝ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጋዥ ነው። መልሶችን ይጠይቁ፣ መልሶችን ያግኙ፣ ቋንቋዎችን ይተርጉሙ እና ሌሎችም።
የብሬቭ መፈለጊያ
የብሬቭ መፈለጊያ በዓለም ላይ በጣም የተሟላ ፣ ገለልተኛ ፣ ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ የበይነመረብ መረጃ መፈለጊያ ነው።
ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ የበይነመረብ መረጃ መፈለግ
ብሬቭን በመጠቀም ደህንነትዎን ጠብቀው እና በበለጠ ሚስጥራዊነት ድረ ገጾችን ይፈልጉ። ብሬቭ ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ የበይነመረብ አጠቃቀም እንዲኖርዎ በትኩረት ይሰራል።
የበይነመረብ መረጃን በፍጥነት ይፈልጉ
ብሬቭ ፈጣን የበይነመረብ መረጃ መፈለጊያ ነው! ብሬቭ የገጽ ማሳያ ጊዜን ይቀንሳል፣ የድረ ገጽ ማሰስ ክንውንን ያሻሽላል፤ እንዲሁም በማልዌር የተያዙ ማስታወቂያዎችን ያግዳል።
ሚስጥራዊነትን መጠበቅ
እንደ HTTPS Everywhere (የተመሰጠረ የውሂብ ትራፊክ)፣ የስክሪፕት እገዳ፣ የኩኪ እገዳ እና የግል ማንነት የማያሳውቅ ትሮችን በመሳሰሉ ፈር ቀዳጅ የሚስጥራዊነት እና የደህንነት መጠበቂያ ባሕሪያት የተጠበቀ ነው። በበይነመረብ ግንኙነት ወቅት ክትትል እንዳይደረግብዎ ህጋዊ መብቶችዎን ለማረጋገጥ፣ የአለም አቀፍ የሚስጥራዊነት ቁጥጥር በመደበኛነት እንዲሰራ ተደርጓል።
ብሬቭ ሪዋርድስ
በቀድሞው የድረ ገጽ አሳሽዎ ማስታወቂያዎችን በማየት በይነመረብን ለማሰስ ክፍያ ከፍለዋል። አሁን፣ ብሬቭ ወደ አዲሱ በይነመረብ እንኳን ደህና መጡ ይልዎታል። ጊዜዎ ዋጋ የሚሰጥበት፣ የግል መረጃዎ ሚስጥራዊ ሆኖ የሚቆይበት እና ለእርስዎ ትኩረት የሚሰጥበት ቦታ ነው።
ስለ ብሬቭ
የኛ ተልእኮ ለይዘት ፈጣሪዎች የማስታወቂያ ገቢ እያሳደግን፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ፈጣን እና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ አሳሽ በመስራት፣ የእርስዎን ግላዊነት መጠበቅ ነው። ብሬቭ በማይክሮ ክፍያዎች እና አዲስ የገቢ መጋራት መፍትሄ አማካኝነት በተጠቃሚዎች እና አዘጋጆች መካከል የተሻለ ስምምነት እንዲኖር በማድረግ፣ የመስመር ላይ የማስታወቂያ ስነ-ምህዳሩን ለመለወጥ ያለመ ነው።
ስለ ብሬቭ የበይነመረብ ማሰሻ የበለጠ ለማወቅ፣ እባክዎ ወደ www.brave.com ይሂዱ።
ጥያቄዎች አሉዎት/ድጋፍ ይፈልጋሉ?
በ http://brave.com/msupport ላይ ያግኙን። ከእርስዎ መስማት እንወዳለን። እርስዎ መስማት እንወዳለን።
የአጠቃቀም ውል እዚህ ላይ ይገኛል፡- https://brave.com/terms-of-use/
የሚስጥራዊነት መመሪያ እዚህ ላይ ይገኛል፡- https://brave.com/privacy/
ማስታወሻ፡- አንድሮይድ 7 እና ከዚያ በላይ የሆነን ይቀበላል።
ለአንድሮይድ ምርጡን የግል የድረ ገጽ አሳሽ መተግበሪያ ዛሬ ያውርዱ! ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ በይነመረብን በራስ መተማመን ያስሱ።